ወደ ስርዓተ ጾታ እና ኮቪድ-19 የዳሰሳ ጥናት የሚወስደውን ተስፈንጣሪ አገናኝ ስለከፈቱ እናመሰግናለን፡፡ ይህ የዳሰሳ ጥናት - የሰብአዊነት ጾታ የምርምር ጥናት (Humanitarian Gender Study) - አንድ አካል ሲሆን፣ ጥናቱ ቦስተን፣ ማሳቹሴትስ፣ ዩኤስኤ ውስጥ በሚገኘው በሀርቫርድ የህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ የህክምና ምርምር ማዕከል በሆነው፣ በቤተ እሰራኤል የዲያቆኒት ህክምና ማዕከል (ቢአይዲኤምሲ) የሚካሄድ ነው፡፡

ምርምሩ የሚያተኩረው በሰብአዊነት ዘርፍ (Humanitarian Sector) ላይ በጾታ አድልዎ ዙሪያ ነው፡፡ ምርምሩ በውስጡ በአለምአቀፍ የህዝብ ሰብአዊነት ባለሙያዎች (Humanitarian Practitioners) ላይ ሁለት ጥናቶች ያካትታል፡፡ ይሄኛው ጥናት በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ወቅት በስራ ቦታ ላይ ስላለ የጾታዊ ጥቃት እና ምላሹ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ሌላኛው በስራ ቦታ ላይ ስለሚኖር ጾታዊ መድልዎ ላይ ያተኮረ ጥናት ሲሆን ለወደፊት ፕሮግራሞች/ስራዎች ግብዓት ሊሰጡ የሚችሉ ጥያቄዎች ተካተውበታል፡፡

እያንዳንዱን ጥናት ለማጠናቀቅ ከ20-30 ደቂቃ ሊፈጅቦት ይችላል፡፡ በአንዱ ወይንም በሁለቱም ጥናቶች ውስጥ ለመሳተፍ መምረጥ ይችላሉ፡፡ በጥናቱ ዙሪያ ቃለ-መጠይቅ ለመስጠት ወይንም በቡድን ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ካሎት ምርጫዎን ቢያሳውቁን እኛ እናገኞታለን፡፡

የሁለተኛውን ጥናት ተስፈንጣሪ አገናኝ እንድናጋራዎ እና በቃለ-መጠይቅ ወይንም በቡድን ውይይት ለመሳተፍ ፍላጎት ካሎት እርሶን ለማግኘት እንዲረዳን የኢሜይል አድራሻዎን እንጠይቆታለን፡፡ የመረጃ ትንተና (Data Analysis) ከመካሄዱ በፊት ኢሜይል አድራሻዎ ከመረጃዎ ላይ ይሰረዛል፣ ይህም መረጃው ከባለቤቱ ጋር በቀጥታ እንዳይያያዝ ያደርገዋል፡፡ ኢሜይል አድራሻዎ ለሶስተኛ ወገን ጋር አይጋራም፡፡ የመረጃዎን ሚስጥራዊነት እና ደህንነት እንጠብቃለን፡፡ መረጃው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የሚቀመጥ ሲሆን በየትኛውም የምርምሩ ውጤት እርሶን ማወቅ አይቻልም፡፡

ተሳትፎ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ እርስዎ ጥናቱን በፈለጉበት ሰአት ማቆም ይችላሉ፡፡ በየትኛውም ሰአት ጥናቱ ላይ ያሎትን ተሳተፎ ማቆም ከፈለጉ፣ አቁመው እስከሄዱበት ጊዜ ድርስ የተሰበሰበው የግል መረጃዎ ይቀመጥና የጥናቱን ጥራት ለማስጠበቅ እና/ወይንም ሌሎች የመረጃ ደህንነት እና የግለኝነት ህጎች በሚፈቅዱት መሰረት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ጥናቱ ለእርሶ ቀጥተኛ የሆነ ጥቅም ባያስገኝሎትም፣ ውጤቶቹ ወደፊት የሰብአዊነት ፕሮግራሞች/ስራዎች (Humanitarian Programming) ለማጠናከር እና በሰብአዊነት የስራ ቦታዎች (Humanitarian workplace) ላይ የጾታ እኩልነትን ለማሻሻል ሊረዱ ይችላሉ፡፡ ጥናቱ ላይ መሳተፎ ምንም ወጪ አያስወጣዎም፡፡ ጥናቱን ለማጠናቀቅ ላሳለፉት ጊዜም ማካካሻ አያገኙም፡፡

በጥናቱ ላይ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ወይም ቅሬታ ካለዎት በቢአይዲኤምሲ ዋና መርማሪ የሆኑትን ዶ/ር ጄኒፈር ስኮት በ jscott3@bidmc.harvard.edu ወይንም +1 617-667-4165 ማግኘት ይችላሉ፡፡ በጥናቱ ላይ የማይሳተፍ ሰው ማናገር ከፈለጉ በቤተ-እስራኤል የዲያቆኒት ህክምና ማዕከል የሰዎች ጥበቃ ቢሮን በ +1 (617) 975-8500 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለጊዜዎና ተሳትፎዎ እናመሰግናለን!

Page 1 of 10

Loading... Loading...
You have selected an option that triggers this survey to end right now.
To save your responses and end the survey, click the 'End Survey' button below. If you have selected the wrong option by accident and/or wish to return to the survey, click the 'Return and Edit Response' button.